ደህና መጣህ

ለስደተኝነት መጠየቂያ የሚሆን ጠቃሚ ኢንፎርሜሽንና በጀርመን አገር ስደተኝነትን እስከጠየቅህ ድረስ ያለህ መብት።

ይህ ኢንፎርሜሽን ከኢንተርኔት፣ ከመጽሀፍና ከልምድ ተሰብስቦ የተጠናቀረ ስለሆነ በአጠቃላይ ስለ ስደተኝነት አጠያየቅና መብት ያለውን ሁኔታ ለመረዳት ያስችላል ብለን እንገምታለን። በእርግጥ የእያንዳንዱ የስደተኛ ሁኔታ ከሌላው የሚለይ ሲሆን፣ በተጨማሪም ያሉት ቢሮክራሲያዊ አሰራሮች ቀላል ስላልሆኑና ህግን የሚከተሉ ስለሆነ በቀላሉ ለመረዳት ያስቸግራል። ይህም ሆኖ በምንም ዐይነት ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም። ማንኛውም ሰው ህጋዊ መብት አለው። መልካም ዕድል እንመኛለን!

እንዴት አድርጎ ለጥገኝነት ማመልከት ይቻላል?

በማንኛውም የፖሊስ ጣቢያ ማመልከት ትችላለህ። ወይንም ደግሞ በርሊን ከተማ፣ ቱርም መንገድ 21 (Turmstr. 21, 10559 Berlin) የጤናና የማህበራዊ መስሪያ ቤት ማመልከት ትችላለህ። ከዚያ በኋላ ለጥገኛ ጠያቄዎችና እዚህ አገር መጥተው በስራ ለሚሰማሩ ሰዎች ኃላፊነት የተሰጠው የመንግስት መስሪያ ቤት ያንተን ሁኔታ ይከታተላል፣ ያጠናልም። ያንተ ዕድል በዚህ መስሪያ ቤት እጅ የወደቀ ነው ማለት ነው። እዚያ የስደተኝነት ማመልከቻ ደብዳቤህ ይላካል። በመጀመሪያ ደረጃ ስለ ህይወት ታሪክህ ጠለቅ ያለ ጥያቄዎች ትጠየቃለህ። ፎቶ ትነሳለህ፣ አሻራ ትሰጣለህ፤ ከዚያም በኋላ ጥያቄዎችና እንዴትስ ጀርመን አገር እንደገባህ ትጠየቃለህ። የሰጠኸው መልስ ተቀርጾ በኋላ ለትልቁ የቃለ-መልስ ጥይይቅ ያገለግላል። ስለዚህ መጀመሪያ የሰጠኸው ቃለ-መጠይቅ መልስ ከትልቁ ጋር እንዳይቃረን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

ወረቀት ለማግኘት ስንት ጊዜ መጠበቅ ያስፈልጋል ?

አንድ ቁርጥ ያለ መልስ ለማግኘት ረጅም ጊዜ ያስጠብቃል። በመሀከሉ ሁኔታህ እስኪጣራ ድረስ ለመኖር የሚያስችልህ የወረቀት ፈቃድ ይሰጥሃል። ይህም ማለት በዚህ የመኖሪያ ፈቃድ የመጨረሻውን ውሳኔ እስክታገኝ ድረስ መኖር ትችላለህ ማለት ነው። ስድተኝነት ከጠየቅህ ጀምሮ ሶስት ወራት ባለው ጊዜው ውስጥ በዚህ የመኖሪያ ፈቃድ መንቀሳቀስ የምትችለው የጥገኝነት ማመልከቻህን ባገባህበት ከተማ ብቻ ነው። ማመልከቻህ ተቀባይነት ካላገኘ ይግባኝ የመጠየቅ መብት አለህ። ይህንን ማድረግ የምትችለው ግን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ነው።

ቤት ማግኘት ይቻላል ወይ ?

የጥገኝነት ማመልከቻህን ካስገባህ በኋላ ጥገኝነት ጠይቀው መልስ የሚጠብቁ የሚኖሩበት ቦታ እንድትገባ ትደረጋለህ። ይህ የመጀመሪያው ማረፊያ ቦታ ይባላል። የምትላክበት ቦታ መሄድ አለብህ። አንዳንድ ጊዜ የመኖሪያ ቦታው መንደር ውስጥ ነው። በምትኖርበት ቦታ መተኛ፣ ምግብና የተወሰነ የኪስ ገንዘብ ይሰጥሃል። መኖሪያው ቦታ የተጠበቀና ንጽህናም ያለው ነው። የምትኖርበት ቦታ ንጹህ ካልሆነና በስነ-ስርዓትም የማትያዝ ከሆነ አለመስማማትህን መግለጽ ትችላለህ። በተቻለ መጠን ፎቶ ለማንሳትና ልምድህንም በጽሁፍ መልክ አስፍረህ ለሰብአዊ መብት ወይም ጥገኛ ጠያቄዎችን ለሚረዱ ድርጅቶች ማሳየት ትችላለህ። በመጀመሪያው ቦታ ሶስት ወር ነው መኖር የሚፈቀድልህ። በዚህ ሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ከምትኖርበት አካባቢ ወደ ሌላ ቦታ መሄድ ወይም መንቀሳቀስ አይፈቀድልህም። ከዚያ በኋላ ሌላ ቦታ ትላካለህ።የሚያሳዝነው ግን የሚልኩህ ቦታን መምረጥ አትችልም። አዲሱም ቦታ የማደሪያ ቦታና ገንዘብ ይሰጥሃል። ወረቀት ካገኘህ በኋላ መኖሪያ ቦታ መፈልግና የትኛውም ከተማ መኖር ትችላለህ።

የጀርመን ቋንቋ ለመማር እችላለሁ ወይ ?

ወረቀት ካገኘህ በኋላ የቋንቋ ትምህርት ቤት ሄደህ በነጻ መማር ትችላለህ። በጀርመን ምድር ስትኖር ለመግባቢያና የአገሩንም ሁኔታ ለመረዳት የሚያስችልህ ቋንቋ ትማራለህ።ምናልባት ወረቀት ለማግኘት ብዙ የምትጠብቅ ወይም ደግሞ ማመልከቻህ ተቀባይነት የማያገኝ ከሆነ አሁንም ቢሆን የጀርመንን ቋንቋ ለመማር የምትችልበት ሁኔታ በርሊን ውስጥ አለ። በርሊን ከተማ ውስጥ የጀርመንኛን ቋንቋ ልትማር የምትችልባቸው ቦታዎች ተሰበጣጥረው ይገኛሉ። ለማንኛውም ቀደም፣ ብሎ መመዝገብ ጠቃሚ ነው። ማንኛውንም የቋንቋ መማሪያ ቦታዎች በሚቀጥለው ድህረ-ገጽ ማግኘት ትችላለህ።

http://www.netzwerk-deutschkurse-fuer-alle.de/course-overview/

ጀርመን አገር መስራት እችላለሁ ወይ ?

ከሶስት ወር የጥገኝነት ማመልከቻ ጥያቄና ክንውን በኋላ የስራ ፈቃድ እንዲሰጥህ ማመልከት ትችላለህ። የስራ ዕድል የሚሰጥህ ስራውን የሚሰራ ሌላ ከአውሮፓ የጋራ አገር የመጣ ሰው ካለመለከተና፣ የጥገኝነት ጥያቄው ታውቆለት ለመስራት የማይፈልግ ከሆነ ብቻ ነው። ከ15 ወራት ቆይታ በኋላ ደንበኛውን የስራ ፈቃድ ታገኛለህ። ሁኔታህ ከታወቀልህ የመስራትና የመማር መብት አለህ። ስራ ከሌለህ መንግስት በየወሩ 350 € ሲሰጥሀ፣ በተጨማሪም የቤት ኪራይ ይከፍልልሃል።

ዕድሜዬ ከ18 ዐመት በታች ከሆነና ቤተሰብም ከሌለኝ ምን ማድረግ እችላለሁ ?

ዕድሜያቸው ከ18 ዐመት በታች የሆነ የሚኖሩበት ቦታ መተኛ መኖሪያ ይሰጥሃል። እዚያ እየመጡ ሁኔታውን የሚከታተሉ የማሀበራዊ ሰራተኞች(Social Workers) ሁኔታህን ይከታተላሉ። እዚያም ምግብና የተወሰነ ገንዘብ ይሰጥሃል። የቋንቋ ትምህርት ቤት ትላካለህ፤ ከዚያም በኋላ የመማር ዕድል ታገኛለህ። እንደ መካኒክነት የመሳሰሉ ሙያዎችን የመማር ዕድል ታገኛለህ። በሙያው ከሰለጠንክ በኋላ የመስራት ዕድል ታገኛለህ። የሚያሳዝነው ነግር ግን አብዛኛውን ጊዜ ከአገር ቤት ቤተሰቦችህን ማስመጣት አትችልም።

ሀኪም ቤት ወይም ሀኪም ጋ መሄድ ካለብኝ ምን ማድረግ አለብኝ ?

በመጀመሪያው አስራ አምስት ወራት የስደተኝነት ማመልከቻህ ወቅት ውስጥ ሀኪም ጋ ለመሄድ የምትችለው አስቸኳይ የህክምና ዕርዳታ ለማግኘት የምትችልበት ቦታ ብቻ ነው። ለሴቶች ምናልባት እርጉዝ ከሆኑ የሚጠብቁ ወይም ከቦታ ቦታ የሚያጓጉዙ ረዳት ሰዎች ይመደባሉ። ለማስወረድ ለሚፈልጉ ሁኔታው ከታየ በኋላ የማስወረድ መብት አላቸው። በመጀመሪያው የሶስት ወር የእርግዝና ጊዜ ውስጥ ለማስወረድ በጀርመን ምድር ህጋዊ ሲሆን፣ በተጨማሪም እርግዝናው ለጤንነት ከፍተኛ አደጋ የሚያመጣ መስሎ ከታየ ማስወረድ ይቻላል።

የቤተሰቦቼ ጉዳይስ እንዴት ነው ?

የጥገኝነት መብትህ ከታወቀልህ በኋላ ልጅህንም ሆነ ባለቤትህንም ሆነ ባልን የማስመጣት መብት አለህ። ይህ ዐይነቱ ህግ ቤተሰብን የማገናኘት መብት ተብሎ ይታወቃል።

ለዘለዓለም ጀርመን አገር መኖር ይፈቀዳል ወይ ?

ይህ ሊወሰን የሚችለው በምታገኘው የወረቀት ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ዐይነት ሲሆን፣ የአገርህም ሁኔታ ወሳኝ ነው። ከስምን ዐመት ቆይታ በኋላ የጀርመንን ዜግነት ለማግኘት ማመልከት ትችላለህ። ይሁንና ግን የጀርመንን ቋንቋ በደንብ ለመናገር መቻል ሲኖርብህ፣ በተጨማሪም እየሰራህ ራስህንና ቤተሰብህን የምታስተዳደር መሆን አለብህ።

አገር ቤት ውስጥ በፖለቲካ ምክንያት የተነሳ የሰውነት ስቃይ ከደረሰብኝና የፖለቲካ ክትትልም ቢደረግብኝ ምን ማድረግ እችላለሁ ?

የቃለ መጠይቅ መልስ በምትሰጥበት ጊዜ ይህንን ጉዳይ በደንብ መግለጽ አለብህ። ሰለ ሰውነት መጎሳቀል ወይም ፖሊሶች ስቃይ ስለማድረሳቸው ጉዳይ መናገሩ እንደሚከብድ አስቸጋሪ እንደሆን ይታወቃል። ይሁንና ግን ይህንን ጉዳይ በግልጽና በፍጥነት መናገሩ እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው። በፖለቲካ ምክንያት የተነሳ አገር ቤት ውስጥ በመንግስት በሰውነታቸው ላይ ስቃይ የደረሰባቸው ሰዎች በአውሮፓ አንድነት አባል አገሮች ውስጥ ሁኔታቸው በልዩ መልክ ይጠናል።

ሴት ብሆንስ መብቴ ምን ይመስላል ?

በሴቶች ላይ የሚደርሱ ልዩ ሁኔታዎች፣ ለምሳሌ እንደማስገደድና እንዳትወልድ ማስደረግ(sterilization)፣ ወይም ደግሞ የሴቶችን መብት የሚቀናቀኑ ልማዶች፣ ለምሳሌ የማያስፈልግ ቅጣት ወይም በግዴታ ማጋባትና መግረዝ እነዚህን የመሳሰሉት ሁሉ የጥገኝነት መጠየቂያ ምክንያቶች ይሆናሉ። የአገርሽ መንግስት እነዚህን ሁኔታዎች የማይከታተል ከሆንና ህጉም የሴቶችን መብት የማያስከብር ከሆነ ወይም መንግስት ዝም ብሎ የሚመለከት ከሆነ እነዚህን ሁሉ ማስረዳትና ማረጋገጥ ያስፈልጋል። የጀርመን የጥገኝነት መጠየቂያ ህግ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ያውቃል፣ እነዚህም ለጥገኝነት መጠየቂያ እንደ በቂ ምክንያት ሊያገለግሉ ይችላሉ። ይህንን ቤተሰብህ ባለበት ቦታ ማስረዳት ባይቻል ለጠበቃ ወይም ለመብት የቆመ ድርጅት ማስረዳት ይቻላል።

ምናልባት ሆሞ ሴክሹዋል ወይም ሌዝቢያን ብሆን ምን ማድረግ እችላለሁ ?

በእነዚህ ምክንያት የተነሳ አገር ውስጥ ክትትል የሚደረግብህ ከሆነና እዚያም መኖር ካልቻልክ ጥገኝነት የመጠየቅ መብት አለህ። በአወሮፓው አንድነት ህግ መሰረት ይህ ጉዳይ ለጥገኝነት ጥየቃ እንደ በቂ ምክንያት ይታወቃል። በተለይም የጀኔቫ ኮንቬንሽን ወይም ገለጻ ይህንን ያውቃል። በአገርህ ውስጥ ከፍተኛ ክትትል እንደሚደረግብህና በዚህም የተሰቃየህ መሆንህን ማረጋገጥ አለብህ።

በጀርመን ምድር መጥተው በዚህ ምክንያት ጥገኝነት የሚጥይቁ በአገራቸው ውስጥ ከባድ ስቃይና ካለበቂ ምክንያት ክትትል የሚደረግባቸው መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው።

ጠለቅ ያለ ገለጻ ስለ ጥገኝነት !

ቀድሞውኑ አስከፊ ሁኔታ ከደረሰብህና አገር ቤት ብትመለስ በህይወትህ ላይ አደጋ የሚደርስ ከሆነ ይህ ጉዳይ ለማመለክቻህ ጠቃሚና ወሳኝ ነው። እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ሁኔታዎች በህይወት ላይ አደጋ እንዳላቸውና ለእስራትና ለተጨማሪም ስቃይ የሚያደርሱ መሆናቸው ግንዛቤ ውስጥ ይገባል።ሌሎችም በሰውነት ላይ የሚደርሱ ክትትሎችና የጦርነት ሁኔታዎች ወይም መብት የሚጥስ ጉዳይ እንደ ምክንያት ሊወሰድ ይችላል።

ህጋዊ የሆነ የጥገኝነት ትርጉም ጉዳይ፡ „በዘር፣ በሃይማኖት፣ በጎሳ ክትትልና ወይም በፖለቲካ ዕምነት የተነሳና በዚህም ምክንያት የተነሳ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት አባል ሆኖ ክትትል የሚደረግበት የጥገኝነት መሰረታዊ ሃሳብና ማረጋገጫ ዋና ትርጉም ሆኖ ይወሰዳል።“

የደብሊን ስምምነት !

በደብሊን ስምምነት መሰረት የጥገኝነት መብት ጉዳይና ጥያቄህ በሌላ የአውሮፓ አንድነት አገር የሚጠናው በመጀመሪያ በአረፍክበትና እዚያ በተመዘገብክበት የአውሮፓ አንድነት አገር ወይም በቪዛ መጥተሀ እዚያ የቆየህበት ሁኔታ ጋር በማነፃፀር ነው። በዚህም ምክንይት በደብሊን ስምምነት መጀመሪያ ጥገኝነት የጠየቅህበት ወይም በቪዛ መጥተህ የተመዘገብክበት የአወሮፓው አንድነት አገር እንደገና ተመልሰህ እንድትሄድ ይደረጋል። በአሁኑ ጊዜ ከሲሪያ ለመጡ ጥገኞትና ጀረመን አገር ጥገኝነትን የጠየቁ ሰዎች ይህ ጉዳይ አይመለከታቸውም። ለምሳሌ ወደ ግሪክ እንዲመለሱ አይደረግም። ክንውኑ ወይም ጥናቱ ግን ብዙ ጊዜ ሊወሰድ ይችላል። ለምሳሌ ጥገኝነት የጠየቅህብት የመጀመሪያው የአውሮፓው አንድነት አገር የሚመልሱህ ከሆነና ካሳወቁህ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የይግባኝ ማመልከቻ ማስገባት አለብህ።

የቃለ መጠይቁ ጉዳይስ ?

ለቃለ መጥይቁ በደንብ መዘጋጀት አለብህ። በመጀመሪያ ግን ጠበቃ ጋር ወይም አማካሪ ጋር ለመነጋገር ወይም ለመመካከር ሞክር። ለማንኛውም ታሪክህን በደንብ ለማወቅና ለማስረዳት መዘጋጀት አለብህ። ቀኖችና ዐመታት እንዳይምታቱ በደንብ መዝግባቸው። እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ሃሳቦችና ዓመታት ወይም ቀናት የምትሰጥ ከሆነ ችግር ይፈጠርብሃል። ይህንን ሁኔታ በደንብ አድርገው ነው የሚያዳምጡት። ተጨባጭ የሆኑና ያልተንዛዙ ምክንያቶችን ማቅረቡ ወይም መስጠቱ በጣም ጠቃሚ ነው።በተቻለ መጠን የሚያሳምኑ ማረጋገጫዎች ለማቅረብ መሞከር። በሰውነትህ ላይ የደረሱ ስቃዮች ሁሉ ጠቃሚዎች ናቸው። በተጨማሪም የህክምና ማስረጃዎች፣ ጋዜጣዎችና ከህይወትህ ጋር የተያያዙና የፖለቲካ ድርጅት ወይም የአንድ ጎሳ ወይም ሃይማኖት አባል መሆንህን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ለጥገኝነት በቂ ማስረጃዎች ሆነው ሊወሰዱ ይችላሉ።በተቻለ መጠን አገር ቤት ብትመለስ በህይወትህ ላይ ከፍተኛ አደጋ የሚደርስብህ መሆኑን ለማስረዳት ወይም ለማረጋገጥ ሞክር። ለምን ጀርመን መብትህን የምታስከብርበትና ካለ አደጋ መኖር የምትችልበት አገር መሆኑን ለማሳየት መሞከር አለብህ።

በጥያቄው ምልልስ ጊዜ በቂ ሰዓት ለመውሰድ ሞክር። እረፍትም ጠይቅ። ጥያቄውም ካልገባህ እንደገና እንዲገለጽልህ ጠይቅ። በነፃ ለመናገር ሞክር። አትፍራ፣ አትደናገጥም። ካስተርጓሚህ ጋር ችግር ካለብህ ለመናገር ሞክር። ሴቶች በሴቶች የመጠየቅና አስተርጓሚያቸውም ሴቶች እንዲሆኑላቸው የማመልከት መብት አላቸው። በመጨረሻ ላይ መፈረም ያለብህ በሰጠኸው መልስ ከተደሰትክና አጥጋቢም መልስ ሆኖ ከታየኽና ስህተትም ከሌለበት ብቻ ነው። ቅጅ(ኮፒ) ለማግኘት የመየቅ መብት አለህ። በመልስህና በጥያቄህ ካልተደሰትክ ከጠበቃህ ወይም ካማካሪህ ጋር ተመካከር።

የጥገኝነት ማመልከቻዬ ከታወቀልኝ በኋላስ ምን ይሆናል ?

የጀርመን አገር መኖሪያ ካለህ የጀርመንኛ ቋንቋን የመማር ዕድል ይኖርሃል። ቋንቋውን እያሻሻልክ ስትሄድ ስራ የማግኘት ዕድልህም ከፍ ይላል። ስራ እስክታገኝ ድረስ ከመንግስት ራስህን መደጎሚያ ገንዘብ ታገኛለህ። ወደ ሌሎች የአውሮፓ አገሮች እየተዘዋወርክ ለማየት ትችላለህ፤ ነገር ግን እዚያ መኖርና መስራት አይፈቀድልህም።

የጥገኝነት ማመልከቻው ዕውቅናን ካለገኘስ ምን ይሆናል ?

ማመልከቻው ተቀባይነት ካላገኘ የፌዴራል መንግስቱ ደብዳቤ ይጽፍልሃል። የይግባኝ መብት አለህ። ይህንን ማድረግ ያለብህ ግን ደብዳቤው እንደደረሰህ ከአንድ ሳምንት እስከሁለት ሳምንት ባለው ጊዜው ውስጥ ነው። ለዕርዳታም ማመልከት ትችላለህ። ይሁንና ላይሰጥህ ይችላል። እስክትባረር ድረስ አንድ ቦታ ተዘግተህ ትቆያለህ።

ምናልባት ለጊዜው እንድትቆይ መደረግ ብትችልም፣ ይህም ማለት ተቀባይነት የለህም ማለት ነው። መታወቂያም ስለሌለህ ወደ አገርህ እንኳ ቢመልሱህ የአገርህ መንግስት አልቀበልም ሊልህ ይችላል። ይህ የአጭር ጊዜ ስምምነት ሲሆን ጊዜው ለብዙ ዐመታት ሊራዘም ይችላል። ስራ ለመስራት ፈቃድ ብታገኝም በመጀመሪያው አራት ዐመታት ስራ ለማግኘት በጣም ይቸግርሃል። ስራ ለማግኝት ትችል ዘንድ ተጨማሪ ስልጠና ሊሰጥህ ይችላል። ጥገኝነት የማግኘት ዕድሉ በጣም ዝቅ ካለ አንድ አውሮፓዊት ማግባቱ የመኖሪያ ፈቃድ ሊያሰጥህ ይችላል።

ምናልባት ፖሊስ መታወቂያ ቢጠይቀኝስ ምን እሆናለሁ ?

ጀርመን አገር መንገድ ላይ ስትዘዋወር ፖሊሲ ቢያጋጥምህ መታወቂያ የመጠየቅ መብት አለው። መታወቂያ ከሌለህ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ ምርመራ በማድረግ ማንነትህን ለማረጋገጥ ይሞክራል።ይሁንና ግን ከ12 ሰዓት በላይ ፖሊስ ጣቢያ የማቆየት መብት የለውም።

ብትታሰርስ ዕጣህ ምን ይሆናል ?

ለምን እንደታሰርክ የማወቅ መብት አለህ። መብት እንዳለህ የሚያሳይ ደኮሜንት ይቀርብልሃል። የጀርመንኛ ቋንቋ የማትችል ከሆነ አስተርጓሚ እንዲያስረዳህ ይደረጋል። ለዚህ አስተርጓሚ እንዲቀርብልህ ጠይቅ። በዚህን ጊዜ መብትህን እንደተረዳህ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንድትፈርም ይደረጋል። በተጨማሪም አስተርጓሚ የማግኘትና፣ ስልክም የመደወል በዚያውም መሰረት ጠበቃና ሀኪም ጋር የመገናኘት መብት አለህ።

ወረቀት ሳይኖር እንዴት መኖር ይቻላል ?

የተወሰኑ ሰዎች ፈቃድ ሳይኖራቸው ጀርመን አገር ይኖራሉ። አንዳንዶች ለስራ ሲሉ በምስጢር ይመጣሉ።ሌሎች የመኖሪያ ፈቃድ ለተወሰነ ጊዜ ካላቸው በኋላ አይራዘምላቸውም። አንዳንዶች ደግሞ ጥገኝነት ከጠየቁ በኋላና ሳይታወቅላቸው ሲቀር ይደበቃሉ። ካለህግ የሚኖሩ ሰዎች ኑሮ በጣም ከባድ ነው። ምክንያቱም ከመንግስት የገንዘብና የህክምና ዕርዳታ ለማግኝት የመጠየቅ መብት የላቸውም። ስለሆነም በድብቅ ሲሰሩ በጣም ይበዘብዛሉ።

በተጨማሪ የበለጠ ኢንፎርሜሽን ለማግኘት የሚቀጥለውን ድህረ-ገጽ ተመልከት

www.w2eu.info

ምክርና ኢንፎርሜሽን የሚገኝባቸው አድራሻዎች

KUB – ኢንፎርሜሽን ሴንተር በተለያዩ ቋንቋዎች የህግ እማካሪዎች ምክር የሚስጡበት አድራሻ

ስልክ ቁጥር 030 614 94 00 + 030 614 94 04,

ቢሮአችን አገልግሎት የሚስጥበት ቀን ስኞ ማክስኞ ሃሙስ አና እርብ ከጠዋቱ 10-13 ሰአት ነው

አድራሻችን: Oranienstrasse 159, 10969 Berlin (Moritzplatz አጠገብ)

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.kub-berlin.org

ኢሜይል አድራሻች: kontakt@kub-berlin.de

Al Muntada – ከአረብ አገር ለሚመጡ ሰዎች

ስልክ ቁጥር: 030 68 24 77 19

ቢሮአችን አገልግሎት የሚስጥበት ቀን ማክስኞ 10-13 ሰአት ነው ሃሙስ 14-17 ሰአት ነው

አድራሻችን: Morusstrasse 18 A, 12053 Berlin

ኢሜይል አድራሻች: almuntada@diakoniewerk-simeon.de

Asyl in der Kirche Berlin – ለቤተክርስቲያን ጥገኝነት ለምትጠይቁ

ስልክ ቁጥር: 030 691 41 83

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.kirchenasyl-berlin.de/

Beratungstelle für Migrantinnen und Migranten von Arbeit und Leben – ህግን ስራን እና አኗኗርን

በተመለከአተ አማካሪዎች እና ረዳቶች የሚገኙበት ቦታ

ስልክ ቁጥር: 030 40 39 92 56

አድራሻችን: Keithstrasse 1-3, 10787 Berlin

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.berlin.arbeitundleben.de/kontakt.html

Flüchtlingsrat Berlin e.V. – በበርሊን የጥገኞችእ ጉዳይ አስፈጳሚ

አድራሻችን: Georgenkirchstrasse 69-70 ,10249 Berlin

ስልክ ቁጥር: 030 243 44 57 62

ኢሜይል አድራሻች: buero@fluechtlingsrat-berlin.de

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.fluechtlingsrat-berlin.de

Migrationsrat Berlin-Brandenburg – ኢንፎርሜሽን ለጥገኞች

አድራሻችን: Oranienstrasse 34, 10999

(U Kottbusser Tor አጠገብ), አውቶቡስ ቁጥር M29 (የመውረጃ ቦታ Adalbertstrasse/Oranienstrasse)

ቢሮ ስልክ ቁጥር: 030 61658755, የአማካሪኢ ስልክ ቁጥር : 030 60031139

ኢሜይል አድራሻች: info@mrbb.de

PRO ASYL – ለጥገኞች እርዳታ ሰጪ ድርጅት

ስልክ ቁጥር: 030 69230688

ኢሜይል አድራሻች: proasyl@proasyl.de

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.proasyl.de

……………………………………………………………………………………………..

እድሜያቸው ከ18 አመት በታች ለሆነ

AKINDA – አርዳታ እና አንክብካቤ

ስልክ ቁጥር: 030 32 70 93 40

አድራሻችን: Paulsenstrasse 55-56, 12163

ኢሜይል አድራሻች: akinda@xenion.org

ኢንተርኔት አድራሻች: http://xenion.org/angebote/akinda/

Alafia e. V – አርዳታ እና አንክብካቤ

ስልክ ቁጥር: 030 45 60 64 16

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.alafia-kinderrechte.de/deutschland/

BBZ – አርዳታ እና አንክብካቤ ሰጪ ድርጅት

ስልክ ቁጥር: 030 666 407 20, 030 666 407 23

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.bbzberlin.de/

አድራሻችን: Turmstrasse 72, Floor 4, 10551 Berlin

…………………………………………………………………………………………….

ለሴቶች ብቻ

S.U.S.I. የጤና የጭንቀት አና የሶሻል ቸግር ላለባቸው

ስልክ ቁጥር: 030 78 95 93 94

አድራሻችን: Innsbrucker Strasse 58

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.susi-frauen-zentrum.com/ (+ Facebook)

SOLWODI – በትዳር ውስጥ ቸግር ላለባቸው ከፍላጎት ውጪ ትዳር መስርተው ለመጡ

ስልክ ቁጥር: 030 81 00 11 70

አድራሻችን: Kranoldstrasse 24

ኢሜይል አድራሻች: berlin@solwodi.de

BIG Hotline – ለሚደበደቡ ሴቶቸ አርዳታ ሰጪ

ስልክ ቁጥር: 030 61 10 30 0 በማንኛውም ሰአት [24] ሰአት

Ban Ying e.V. – በትዳር ውስጥ ቸግር ላለባቸው ከፍላጎት ውጪ ትዳር መስርተው ለመጡ

አድራሻችን: Anklamer Strasse 38, 10115 Berlin

ስልክ ቁጥር: 030 440 63 73 + 030 440 63 74

ኢሜይል አድራሻች: info@ban-ying.de

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.ban-ying.de

BAIP – አማካሪ ከአፍሪካ አገር ለሚመጡ ሴቶች

አድራሻችን: Karl-Marx-Strasse 42, 12043 Berlin

ስልክ ቁጥር: 030 62 72 93 30

TIO – ለትምህርት እና ስራ ለማግኘት እርዳታና ኢንፎርሜሽን የሚሰጥ ድርጅት

አድራሻችን: Reuterstrasse 78, 12053 Berlin

ስልክ ቁጥር: 030 624 10 11

ኢሜይል አድራሻች: tio-qualifizierungsprojekt@t-online.de

…………………………………………………………………………………………

ሴት ለሴት አና ወንድ ለወንድ [የግብረሰዶም] ግንኙነት ላላቸው አርዳታ ሰጪ ድርጅት

LesMigraS – ሴት ለሴት አና ወንድ ለወንድ [የግብረሰዶም] ግንኙነት ላላቸው አርዳታ ሰጪ ድርጅት

አድራሻችን: Kulmer Strasse 20a, 10 783 Berlin

ስልክ ቁጥር: 030 21 91 50 90

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.lesmigras.de/

ኢሜይል አድራሻች: info@lesmigras.de

MILES des LSVD Berlin – ሴት ለሴት አና ወንድ ለወንድ [የግብረሰዶም] ግንኙነት ላላቸው አርዳታ ሰጪ ድርጅት

አድራሻችን: Kleiststrasse 35, 10787 Berlin

ስልክ ቁጥር: 030 22 50 22 15

ኢንተርኔት አድራሻች: https://berlin.lsvd.de/projekte/miles/

ኢሜይል አድራሻች: miles@blsb.de

Café Kuchus – ሴት ለሴት አና ወንድ ለወንድ [የግብረሰዶም] ግንኙነት ላላቸው አርዳታ ሰጪ ድርጅት

አድራሻችን: Wilhelmstrasse 115, 10963 Berlin-Kreuzberg,

ቢሮአችን አገልግሎት የሚስጥበት ቀን ማክሰኞ ወይም አርብ ከ 14-18 ስአት

ኢንተርኔት አድራሻች: https://www.schwulenberatungberlin.de/wir-helfen/queere-fluchtlinge/

………………………………………………………………………………………………

የጤንነት ችግር ላለባቸው

Malteser Migranten Medizin – የመታከሚያ ካርድ ለሌላቸው ስደተኞች

አድራሻችን: Aachener Strasse 12, 10713 Berlin-Wilmersdorf

(U-Bahn & S-Bahn: Heidelberger Platz አጠገብ), አውቶቡስ ቁጥር 101 የመውረጃ ቦታ: Paretzer Straße, አውቶቡስ ቁጥር 249 የመውረጃ ቦታ: Brabanter Platz

ስልክ ቁጥር: 030 82 72 26 00

ቢሮአችን አገልግሎት የሚስጥበት ቀን ማክሰኞ እሮብ እና አርብ ከ 9-15 ስአት

ኢሜይል አድራሻች: MMMedizin@malteser-berlin.de

Büro für Medizinische Flüchtlingshilfe – የመታከሚያ ካርድ እና የመኖሪያፈቃድ ለሌላቸው ስደተኞች

አድራሻችን: Mehringhof, Gneisenaustrasse 2A, ቢሮአችን ከሁዋላ የሚገኘው ሕንፃ ውስጥ ነው,

10969 Kreuzberg

U-Bahnhof Mehringdamm አጠገብ

ስልክ ቁጥር: 030 69 46 746

ቢሮአችን አገልግሎት የሚስጥበት ቀን ሰኞ ወይም ሀሙስ ከ 16.30 – 18.30 ነው

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.medibuero.de

ኢሜይል አድራሻች: info@medibuero.de

BzFO – በፓለቲካ ምክንያት ሥቃይ መከራና ችግር ለደረሰባቸው

አድራሻችን: Paulsenstrasse 55-56

ስልክ ቁጥር: 030 30 39 060

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.bzfo.de/homeen.html

ኢሜይል አድራሻች: mail@bzfo.de

Xenion- በፓለቲካ ችግር ምክንያት የአእምሮ ህመም ላለባቸው

ስልክ ቁጥር: 030 32 32 933

ኢንተርኔት አድራሻች: http://xenion.org

ኢሜይል አድራሻች: info@xenion.org

Berliner Rotes Kreuz – ቀይ መስቀል

አድራሻችን: Bachestrasse 11, 12161 Berlin

ስልክ ቁጥር: 030 85 00 50

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.drk-berlin.de

…………………………………………………………………………………………….

EXTRA

KUBየጀርመንኛ ቋንቋ ትምህርት በነፃ የሚሰጥበት ድርጅት

አድራሻችን: Oranienstrasse 159, 10969 Berlin

ስልክ ቁጥር: 030 614 94 00

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.kub-berlin.org/index.php/en/german-classes/164-german-courses

Start with a friendአገልግሎት እና ጉዳይ የሚያስፈጽሙ ግለሰቦች የሚገኙበት አድራሻ

ኢንተርኔት አድራሻች: http://www.start-with-a-friend.de/refugees

Café Engels – የእንግሊዘኛ ቋንቋ ለስደተኞች

አድራሻችን: Herrfurthstrasse 21

U-Bahn Boddinstrasse አጠገብ ነው

ቢሮአችን አገልግሎት የሚስጥበት ቀን ማክሰኞ 18 20 ነው

ቤተሰብ ለጠፉባቸው የሚያፋልጉ አርዳታ ሰጪ ድርጅት

ኢንተርኔት አድራሻች: https://www.facebook.com/searchandfindrefugees

ኢንተርኔት አድራሻች: http://familylinks.icrc.org/europe/en/Pages/home.aspx

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s